የስኳር ምርመራ ጥቅሎች (Diabetes Screening packages)

Creative conceptual image of diabetes awareness with pink letters on purple background.

ጊዜዎ ወርቅ ነው – ጤናዎንም በቅልጥፍና ይመርመሩ

ጊዜ ወርቅ በሆነበት በዚህ ዘመን፣ ስለ ጤናችን ለማወቅ ከአንዱ ቀጠሮ ወደ ሌላው መባዘን፣ ውጤት ለመጠበቅ ቀናትን መቁጠር እና የተበታተኑ መረጃዎችን ለማገናዘብ መጨነቅ አያስፈልግም።
በተለይም እንደ ስኳር እና የልብ ህመም ያሉ ወሳኝ ጉዳዮች ላይ።

ለዚህ በመመርኮዝ፣ ጥራትን እና ቅልጥፍናን ያጣመሩ 3 ልዩ የስኳር ምርመራ ጥቅሎች አዘጋጅተናል።
ሁሉም ጥቅሎች የቅድሚያ አገልግሎት (Priority Service)፣ የላብራቶሪ እና የምስል ምርመራዎችን ከስፔሻሊስት ሃኪሞች ጋር የሚደረግ ምክክር ያካትታሉ።

(Diabetes Essential Monitoring Package)

ለማን ይመከራል?

  • የስኳር ምርመራ ለመጀመር ለሚፈልጉ
  • ለስኳር ህመም አጋላጭ ሁኔታ ላላቸው፣ እነሱም፦
    • በቤተሰብ ውስጥ የስኳር ታሪክ
    • ከመጠን በላይ ክብደት (Overweight)
    • ጤናማ ያልሆነ አመጋገብ
    • ለረጅም ጊዜ አለመንቀሳቀስ
    • ዕድሜ ከ 35 ዓመት በላይ
    • ከፍተኛ የደም ግፊት
    • የተዳከመ የግሉኮስ መቻቻል (IGT)
    • በእርግዝና ወቅት የስኳር ታሪክ

(Diabetes & Heart Complete Package)

የስኳር ህመም በልብ ላይ ያለው ተፅዕኖ ከፍተኛ ነው።

ለማን ይመከራል?

  • የስኳር ታካሚዎች ሆነው የልብ ጤናቸውን ለማረጋገጥ
  • የስኳር ታካሚዎች ሆነው ለልብ ህመም አጋላጭ ሁኔታዎች ላላቸው፣ እነሱም፦
    • ከፍተኛ የደም ግፊት
    • ሲጋራ ማጨስ
    • ከመጠን በላይ መወፈር
    • የአካል እንቅስቃሴ አለመኖር
    • ጤናማ ያልሆነ አመጋገብ
    • ከመጠን በላይ አልኮል መጠጣት

(Diabetes Complication Screener Package)

ለማን ይመከራል?

  • ደካማ የሆነ የስኳር ቁጥጥር ላላቸው የስኳር ታካሚዎች

ይህ ጥቅል፣
👉 የአይን
👉 የኩላሊት
👉 የፔሪፌራል ኒውሮፓቲ
👉 የደምስር ችግሮች
መኖር አለመኖራቸውን ቀድሞ ያረጋግጣል።

የነገ ጤናዎን ዛሬውኑ ይወቁ

ላንድማርክ አጠቃላይ ሆስፒታል

📍 አድራሻ
ከሜክሲኮ ወደ ቄራ በሚወስደው መንገድ፣ ከገነት ሆቴል ከፍ ብሎ

📞 ለቀጠሮ እና መረጃ
0115-52-57-19 | 0115-52-54-63

🔗 ለጥቅሎቹ ዝርዝር መረጃ እና ቀጠሮ ሊንኩን ይጫኑ


Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *