የስኳር ህመምን ለመቆጣጠር፣ የተወሳሰቡ የጤና ችግሮችን ለመከላከል እና ጤናማ ህይወት ለመምራት በባለሙያዎች የተዘጋጁ ልዩ የምርመራ ጥቅሎቻችንን ይመልከቱ።
1. Diabetes Essential Monitoring (ጥንቁቅ የስኳር ምርመራ ጥቅል)
ይህ ጥቅል ለማንኛውም የስኳር ምርመራ ማድረግ ለሚፈልግ ሰው እና የስኳር ህመም አጋላጭ ሁኔታዎች (ከመጠን በላይ ውፍረት፣ የቤተሰብ ታሪክ፣ ወዘተ) ላለባቸው ሰዎች የተዘጋጀ መደበኛ የክትትል ጥቅል ነው።
ጥቅሉ የሚያካትታቸው ዋና ዋና ምርመራዎች፡-
-
የሃኪም ምክክር፡ በስፔሻሊስት ሃኪም የሚደረግ ዝርዝር ምርመራ።
-
የስኳር መጠን ምርመራ፡ በባዶ ሆድ (FBS) ወይም ከምግብ በኋላ (RBS)።
-
HbA1C (የ3 ወር አማካይ)፡ የህክምናውን ውጤታማነት ለመገምገም የሚያገለግል ተመራጭ (Gold standard) ምርመራ።
-
የኮሌስትሮል ምርመራ፡ ለልብና ደም ቧንቧ ጤንነት።
-
የኩላሊትና ጉበት ምርመራ፡ ከስኳር ህመም ጋር ተያይዘው የሚመጡ የኩላሊት እና የጉበት ስብ (NAFLD) ችግሮችን ለመለየት።
-
የታይሮይድ ምርመራ፡ ሜታቦሊዝምን የሚያዛባ የሆርሞን ችግር መኖር አለመኖሩን ለማወቅ።
-
ኢሲጂ (ECG) እና የሆድ አልትራሳውንድ፡ የልብ ምት እና የጉበት ጤንነት ቅኝት።
-
የደም ግፊትና BMI፡ አጠቃላይ የሰውነት አቋም ክትትል።
-
የሆድ አልትራሳውንድ – በጉበት ላይ የሚጠራቀም ስብን ለመመርመር የሚደረግ ቅኝት
ልዩ የምክክር እና የድጋፍ አገልግሎቶች፡-
የአመጋገብ ምክር፡ እንደየግለሰቡ የሚዘጋጅ፣ ባህላዊ ምግቦችን ያካተተ የምግብ ዕቅድ (Personalized Meal Plan)።
የእግር ምርመራ፡ የነርቭ ጉዳት እና ቁስል ቅድመ ምርመራ።
ስልጠና: የስኳር መለኪያ መሳሪያን በቤት ውስጥ እንዴት መጠቀም እንዳለቦት የሚሰጥ በተግባር የተደገፈ ስልጠና።
ሪፖርት: የህክምና ማጠቃለያ ሪፖርት (Medical Summary)።
2. Diabetes & Heart Complete (የተሟላ የስኳርና ልብ ምርመራ ጥቅል)
የስኳር ህመም በልብ ጤንነት ላይ የሚያደርሰውን ተጽእኖ ለመቆጣጠር ለሚፈልጉ እና ለልብ ህመም አጋላጭ ሁኔታዎች (ሲጋራ ማጨስ፣ ውፍረት፣ የደም ግፊት) ላለባቸው የተዘጋጀ ጥቅል ነው።
ይህ ጥቅል “ጥንቁቅ ጥቅል” ውስጥ ያሉትን ሁሉንም ምርመራዎች አካቶ ተጨማሪ የልብ ምርመራዎችን ይይዛል፡-
-
Stress ECG (የልብ የጫና ምርመራ): በአካል ብቃት እንቅስቃሴ ወቅት የልብን የደም ፍሰት እና አቅም ይፈትሻል።
-
Echocardiography (የልብ አልትራሳውንድ): የልብ ጡንቻ ድክመት (Diabetic Cardiomyopathy) እና የልብ የመርጨት አቅምን ለመገምገም።
-
Carotid Doppler (የአንገት ደም ስሮች አልትራሳውንድ): ለስትሮክ (Stroke) የሚያጋልጥ የደም ስር መጥበብን ለመለየት።
-
CRP & CBC: አጠቃላይ የሰውነት ውስጥ ብግነት (Inflammation) እና የደም ማነስ ምርመራ።
ልዩ ጥቅማጥቅሞች፡-
-
የልብ ጤና ሪፖርት: ለልብ ህመም ያለዎትን ተጋላጭነት (Cardiac Risk Stratification) በዝርዝር የሚያሳይ ሪፖርት።
-
ጥልቅ የአመጋገብ ምክክር: ልብን የሚጠብቅ ልዩ ሥርዓተ ምግብ ምክር።
3. Diabetes Complication Screener (የስኳርና ተጓዳኝ ህመሞች ምርመራ ጥቅል)
ይህ ጥቅል የስኳር መጠናቸው የተዛባ (Uncontrolled) እና ለተወሳሰቡ የጎንዮሽ ጉዳቶች (ለዓይን፣ ኩላሊት እና ነርቭ ህመሞች) ተጋላጭ ለሆኑ ታካሚዎች የተዘጋጀ ነው።
ጥቅሉ የሚያካትታቸው ዝርዝር ምርመራዎች፡-
-
መሰረታዊ ምርመራዎች: በስፔሻሊስት ምክክር፣ HbA1C፣ የኮሌስትሮል፣ የጉበት እና የኩላሊት ምርመራዎች።
-
Microalbuminuria (የሽንት ምርመራ): በኩላሊት ላይ የሚደርስ ጉዳትን በመጀመሪያ ደረጃ ላይ ለመለየት።
-
Retinal Eye Exam (የዓይን ሬቲና ምርመራ): ለዓይነ ስውርነት መንስኤ የሆነውን የሬቲና ጉዳት (Diabetic Retinopathy) ለመለየት።
-
Vibratory Perception (የነርቭ ምርመራ): በእግር ላይ የነርቭ ጉዳት (Neuropathy) መኖር አለመኖሩን ለመለካት።
-
Doppler Ultrasound: የእግር ደም ስሮች የደም ዝውውር ችግርን ለመመርመር።
-
Renal Ultrasound: የኩላሊት አወቃቀርን፣ ጠጠር ወይም እጢን ለመፈተሽ።
-
ቫይታሚን B12 እና D: ለነርቭ እና አጥንት ጤንነት ወሳኝ የሆኑ ቫይታሚኖችን ለመለካት።
የምርመራ ውጤት ሪፖርት፡-
አጠቃላይ የሪስክ ሪፖርት (Comprehensive Risk Report): በልብ፣ ኩላሊት፣ ዓይን እና ነርቭ ላይ ሊከሰቱ የሚችሉ የጤና ችግሮችን እና ያለዎትን የተጋላጭነት ደረጃ የሚያሳይ ዝርዝር ሰነድ።
ለቀጠሮ እና ለበለጠ መረጃ
ለቀጠሮ እና መረጃ፡ በ 0115-52-57-19 ወይም 0115-52-54-63 ይደውሉ። ወይም በቴሌግራም https://t.me/Landmarhospitalet መልዕክት ያስቀምጡልን።
