World Patient Safety Day 2025 at Landmark General Hospital

World Patient Safety Day 2025 at Landmark General Hospital

Landmark General Hospital proudly hosted the 7th annual World Patient Safety Day under the theme “Safe Care for Every Newborn and Every Child.”

The event was honored by the presence of distinguished guests including H.E. Dr. Mulatu Teshome (Former President of F.D.R.E), H.E. Dr. Kenea Yadeta (Minister of State for Security Advisor to the Prime Minister & MP), Prof. Mesfin Araya (Commissioner, Ethiopian National Dialogue Commission), H.E. Saharela Abudullahi (State Minister, Ministry of Health), Dr. Fahmi Ahmed (WHO Representative), Ato Melkamu Tiruneh (Addis Ababa Health Bureau Representative), Dr. Abbas Hassan (Health System Innovation & Quality Lead Executive Officer, MoH), and Dr. Markos Feleke (President of the Ethiopian Healthcare Federation), alongside professional associations, leaders of health institutions, Landmark staff, patients, and media professionals.


The day featured inspiring speeches, WHO’s 5 Patient Safety Goals presentation, live safety awareness polls, patient testimonials, and an exhibition tour of Landmark General Hospital’s NICU, ICU, OR, and other critical facilities.

This also comes as Landmark General Hospital continues its major expansion project built on global patient safety standards, further strengthening our mission of delivering safer, quality healthcare for all.

This marks the 5th year Landmark General Hospital has hosted this global day reaffirming our commitment to patient-centered, safe, and quality healthcare.

At Landmark General Hospital, Patient Safety is Everyone’s Business!

World Patient Safety Day 2025

World Patient Safety Day 2025

7ኛዉ የዓለም የታካሚ ደህንነት ቀን” በላንድማርክ አጠቃላይ ሆስፒታል ለ 5ኛ ጊዜ በድምቀት ተከበረ!።

አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ – መስከረም 19፣ 2018 – ላንድማርክ አጠቃላይ ሆስፒታል ከጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ጋር በመተባበር “ደህንነቱን የጠበቀ የጤና ክብካቤ ለሁሉም ጨቅላ ህፃናት እና ህፃናት” በሚል መሪ ቃል 7ኛውን ዓመታዊ የዓለም የታካሚዎች ደህንነት ቀን በዓል በድምቀት አክብሯል።

በዝግጀቱ ላይ የቀድሞ የኢፌዴሪ ፕሬዝደንት ክቡር ዶ/ር ሙላቱ ተሾመ፣ የጠቅላይ ሚኒስትር ደህንነት አማካሪ ሚኒስተር ዴታና የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል ክቡር ዶ/ር ቀንአ ያደታ ፣ የኢትዮጵያ የምክክር ኮሚሽን ኮሚሽነር ፕ/ር መስፍን አርአያ ፣ የጤና ሚኒስቴር ዴታ ክብርት ሰሀረላ አቡዱላሂ ፣ የዓለም ጤና ድርጅት ተወካይ ዶ/ር ፋህሚ አህመድ ፣የአዲስ አበባ ጤና ቢሮ ተወካይ አቶ መልካሙ ጥሩነህ፣ የኦሮሚያ ጤና ቢሮ ኃላፊ ፕ/ር ነፃነት ወርቅነህ ፣ በጤና ሚኒስተር የጤና ስርዓት ኢኖቬሽንና ጥራት መሪ ስራ አስፈፃሚ ዶ/ር አባስ ሐሰን ፣ የኢትጵያ ጤና ክብካቤ ፌድሬሽን ፕሬዝደንት ዶ/ር ማርቆስ ፈለቀ ፣ እንዲሁም የጤና ሙያ ማህበራት ተወካዮች፣ የተለያዩ የመንግስትና የግል ጤና ተቋማት አመራሮችና ተወካዮች፣ጥሪ የተደረገላቸው የላንድማርክ ሆስፒታል ሰራተኞችና ታካሚዎችና የሚዲያ ባለሙያዎች ተገኝተዋል።

የሆስፒታሉ ዋና ስራ አስፈፃሚ ፕሮፌሰር ከበደ ኦሊ ተቋሙ ለአስተማማኝ የህክምና ተግባራት እና ቀጣይነት ያለው መሻሻል ያለውን የማያወላውል ቁርጠኝነት አፅንዖት ሰጥቶ በመስራት በከፍተኛ ኢንቨስትመንት እየተካሄደ ያለውን የማስፋፊያ ፕሮጀክት የአለም አቀፍ የታካሚ ደህንነት መስፈርቶችን ባማከለ መልኩ ለጤና አጠባበቅ ልህቀት ያለውን የረጅም ጊዜ ቁርጠኝነት እንደሚያረጋግጡ ገልፀዋል ። የአለም ጤና ድርጅት ተወካይ ዶ/ር ፋህሚ አህመድ የታካሚዎችን ደህነነት ለማሳለጥና የጤና አጠባበቅ አሰጣጥን ለመምራት የአለም አቀፍ የደህንነት ደረጃዎች እና መመዘኛዎች ያለውን ጠቀሜታ አስምረውበታል።

የአዲስ አበባ ጤና ቢሮን ወክለው የተገኙት አቶ መልካሙ ጥሩነህ በከተማ አስተዳደሩ የታካሚዎች ደህንነት ማስጠበቅ እርምጃዎች አፈጻጸም ላይ ንግግር ያደረጉ ሲሆን የጤና ጥበቃ ሚኒስትር ዴኤታ ሰሀረላ አቡዱላሂ በበኩላቸው መንግስት ለታካሚዎች ደህንነት የሚሰጠውን ትኩረት እንደ ሀገራዊ የጤና እንክብካቤ ቅድሚያ የሚሰጠው መሆኑን አረጋግጠዋል።

በዝግጅቱ የላንድማርክ አጠቃላይ ሆስፒታል ሰራተኞች መልአክት ፣ የሰራተኞች ቁርጠኝነት እና የታዩ የታካሚ ምስክርነቶችን ጨምሮ የላንድማርክ አጠቃላይ ሆስፒታል ለታካሚ ተኮር እንክብካቤ ያለውን ሁለንተናዊ አቀራረብ አጉልተዋል።

በመጨረሻም የሆስፒታሉን የታካሚ ደህንነት-ተኮር መሠረተ ልማት እና የማስፋፊያ ፕሮጀክቶችን በማየት የጨቅላ ህፃናት ከፍተኛ እንክብካቤ ክፍል ፣ የቀዶ ህክምና ክፍል ፣የኩላሊት እጥበት ፣ የምግብ እና የልብስ ማጠቢያ አገልግሎቶችን ጨምሮ የሆስፒታል ማስፋፊያ ስራ ጎብኝተዋል። ዝግጅቱ የታካሚ ደህንነትን በሚመለከት የተዘጋጀውን ኤግዚቢሽን በመጎብኘት ተጠናቋል።

#WorldPatientSafetyDay#PatientSafety#Landmark#LandmarkHospital#maternalandchildhealth

#WorldPatientSafetyDay hashtag#PatientSafety hashtag#SafeCare hashtag#LandmarkGeneralHospital Safe Hospital

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *